post-image

ስለልጅዎ   ትምህርት   ቤት  ጥቂት  እንበልዎ !!

አቤም ዩዝ አካዳሚ ከተመሰረተበት አመት ጀምሮ በህንፃ ግንባታ ጥራትና በቂነት በሰው ሀይል አስተዳደር ፤በተማሪዎች ቅበላ  እነዲሁም በመምህራን ቅጥር ከፍተኛ የሚባል  የሂደት ለውጦችን አካሂዷል፡፡ት/ቤቱ የተነሳበትን አላማ ከግብ እያደርሰ የተማሪዎችን ውጤታማነት እየጨመረ የሰራተኞችንም እድገት በተገቢው ከፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ትምህርት የአንድ አካል ድርሻ ብቻ  አይደለም ፡፡ በመሆኑም አሳታፊ የሆነ  ሥራዎችን ይሰራል የአካባቢውን ማህበረሰብ ወላጆችንና የትምህርት ባለሙያዎችን በያዘ መልኩ ከፍተኛ የሆነ ሁለተናዊ እድገት እያሥመዘገበ ይገኛል ፡፡ በክፍለ ከተማው የተሻለ የመማሪያ ክፍሎችን  ፅዳቱን የጠበቀ የልጆች መጫወቻ ፣ንጹህ የመጸዳጃ ክፍሎች ማራኪ የሆነ የስፖርት ሜዳ  ፣በቂ የመመገቢያ አዳራሽና የሥብሰባ አዳራሽ የተሟላ ላብራቶሪ ፣ምቹና በቂ የሆነ  ቤተመጽሐፍ  የትምህርት ማበልፀጊያ ተጠቃሽ የሆኑ የመማር ማስተማሩን በቀጥታ የሚያግዙ ናቸው፡፡በመሆኑም አስፈላጊ የሚላቸውን ሁሉ ግብዓቶችን በማሟላት ትውልድ ተረካቢ የሆኑ ዜጋዎችን እያፈራ ይገኛል፡፡ከዚህም በተጨማሪ የት/ቤቱን  school mangment system  በማዘመን ማለትም በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ተደርጓል፡፡በመምህራን ተጠናቅሮ የመጣው  የተከታታይ ምዘና ውጤት በቀጥታ በኮምፒውተር ሲስተም በዳታ በማስተካከል የእያንዳንዱን የተማሪ ውጤት ከመምህራን ንክኪ በማስቀረት እያንዳንዱን ትምህርት ከመቶ ያለውን ውጤት አቬሬጅና ደረጃ በሮስተር ሰርቶ የሚያጠናቅቅ ሲስተም ያቀፈ ነው፡፡